መጋቢት 10 2017 - በአዲስ አበባ ንግድ ቤቶችና ትራንስፖርት ሰጭዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ምሽት ሶስት ተኩል እና አራት ሰዓት አገልግሎት መስጠት አለባቸው ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- Mar 19
- 1 min read
በአዲስ አበባ ንግድ ቤቶች እና ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ምሽት ሶስት ተኩል እና አራት ሰዓት አገልግሎት መስጠት አለባቸው ተባለ፡፡
በከተማዋ የኮሪደር ልማት በተሰራባቸው አካባቢዎች ሱቆች እና ሌላም የንግድ አገልግሎት ሰጭዎች እስከ ምሽት በራቸውን እንዳይዘጉ ወይም በራቸው ዝግ ከሆነ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት በራቸው ላይ እንዲያኖሩ የሚያስገድደው ደንብ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ ገብቷል ተብሏል፡፡
ይህን ያለው የከተማዋ ንግድ ቢሮ ነው፡፡

በመንገድ ዳር ያሉ #ንግድ_ቤቶች ፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እስከ ሶስት ሰዓት ተኩል የህዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ደግሞ እስከ 4 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ ደንቡ ያስገድዳል፡፡
ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎችም እስከ ምሽት 4 ሰዓት ሲቆዩ ከተፈቀደው ታሪፍ በላይ ማስከፈል እንደማይችሉ በደንቡ ተደንግጓል፡፡
ይህም ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments