top of page

መጋቢት 10 2017 - በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት መነሻ እና ማረፊያ አቅጣጫዎች ያሉት አዕዋፋት ለአደጋ መከሰት ከፍተኛ ስጋት መሆናቸው ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Mar 19
  • 1 min read

በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት መነሻ እና ማረፊያ አቅጣጫዎች ያሉት አዕዋፋት ለአደጋ መከሰት ከፍተኛ ስጋት መሆናቸው ተነገረ፡፡


አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሔም ተጠይቋል፡፡


የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቭየሽን ባለሰልጣን፣ የአየር መንገድ ሃላፊዎች እና ሌሎችም ለአውሮፕላን አደጋ መከሰት ምክንያት የሚሆኑ #አዕዋፋት መገኛ አካባቢዎች ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል ተብሏል፡፡


የመስክ ምልከታ ከተደረገባቸው ስፍራዎች መካከል ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የሚገኘዉ አድዋ ፓርክ፣ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ደረቅ ቆሻሻ ማቀነባበርያ እና በሸገር ሲቲ ፉሪ ክፍለ ከተማ አካባቢዎች ይገኙበታል።

በእነዚህ ስፍራዎች አዕዋፋት በብዛት አንደሚገኙ ተነግሯል፡፡


ለአዋፋቱ መበራክት ምክንያት የሆኑት ደግሞ ከተለያዩ ፋብሪካዎች፣ ከቄራዎች፣ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ፣ ህገ ወጥ የከብት እርድ የሚካሄድባቸው እና ከመኖሪያ ቤት የሚለቀቁ ፍሳሾች እና ተረፈ ምርቶች መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ተስተውለዋል፡፡


እነዚህ ስፍራዎች ለአየር መንገዱ መነሻ እና ማረፊያ አቅጣጫዎች በመሆናቸው አዕዋፋቱ ለአደጋ መከሰት ከፍተኛ ስጋት በመሆናቸው አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሔ አንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page