የኦሮሚያ ክልል የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በበቂ መጠን ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መሰናክል ሆኗል ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት እየሰራሁ ነው ብሏል።
በአዲስ አበባ የአንዳንድ አትክልቶች ዋጋ ከሠሞኑ ቅናሽ አሳይቷል፤ ለዚህ አንዱ ምክንያት አጎራባች ከሆነው የኦሮሚያ ክልል ምርቶቹ በስፋት ወደ ከተማ እንዲገቡ መደረጉ ነው ተብሏል፡
የኦሮሚያንግድ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ጌሾ ለሸገር እንዳሉት በውሃ እና መሰል ምክንያቶች ቀንሶ የነበረው ምርት አሁን በተሻለ መጠን ወደ ከተማዋ እየገባ ነው ብለውናል።
በኦሮሚያክልል የሚታው የፀጥታ ችግርም አትክልትና ፍራፍሬ በበቂ መጠን ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ለተጠቃሚው እንዳይቀርብ ምክንያት መሆኑ ይነሳል።
ይሄ የፀጥታ ችግርስ ምን ያህል ተሻሽሏል.ያልናቸው የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተውናል።
በክልሉ.የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራትን በአዲስ አበባ ከተማ ካሉት ጋር በማስተሳሰርም፤ የምርት አቅርቦቱ እንዲጨምር እያደረግን ነው ሲሉ አቶ ተስፋዬ ነግረውናል።
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários