top of page

መጋቢት 10፣2016 - የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ እና ቪዛ (VISA) አብረው ለመስራት ተስማሙ

  • sheger1021fm
  • Mar 19, 2024
  • 1 min read

ስምምነቱን የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አሰፋው እና የቪዛ የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ቻድ ፓቮክ ተፈራርመውታል።


የማህበረሰቡን ፍላጎት ያማከሉ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ እንደሚገኝ የተናገረው የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲጂታል ከፍያዎች መሪ ከሆነው VISA ካምፓኒ ጋር ያደረገው ይህ ስትራቴጂካዊ ስምምነት የፋይናንስ አገልግሎትን ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ተብሎለታል፡፡


አጋርነቱ ለብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን በብሄራዊ መታወቂያ የሚሰጡትን የተለያዩ አገልግሎቶች የሚያቀላጥፍ እና የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚያሳድግ ነው ሲባል ሰሞተናል፡፡

ስምምነቱ ምቹና አስተማማኝ የከፍያ ስልትን ለማህበረሰቡ በማቅረብ የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለመፍጠር ለሚደረገው እንቅስቃሴ ታላቅ እርምጃ እንደሚሆን ተፈራራሚዎቹ ተናግረዋል፡፡

12.5 ሚሊዮን በላይ የደንበኞች አሉኝ ያለው የኦሮሚያ ኀብረት ስራ ባንክ በዲጂታል የአገልግሎት ዘርፍ ለሚሰራው ስራ ስምምነቱ በብርቱ እንደሚያግዘው የባንኩ ፕሬዚዳንት አስረድተዋል።


ባንኩ የፋይናንስ ዘርፍ ብዙም ያልደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ በርትቶ እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል።


መሰረቶቼ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደር ማህበረሰብ ናቸው ያለው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ "ምቹ" የተሰኘ ማስያዣ የማይጠየቅበት የዲጂታል ብድር ስርዓት ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ስራ ላይ ማዋሉ ይታወሳል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




תגובות


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page