top of page

መጋቢት 10፣2016 - ለሸማቾች መብት መከበር ይሰራል የተባለ ጥምረት ተመሰረተ

ለሸማቾች መብት መከበር በብርቱ ይሰራል የተባለ ሀገር አቀፍ ጥምረት በይፋ ተመሰረተ።


ሆን ተብሎ ዋጋቸው እንዲጨምር የሚደረጉ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ሲገጥሙ፤ ሸማቹ አልገዛም የሚል አቋም እንዲይዝ እስከማድረግ ጥምረቱ ይሰራል ተብሏል።


ጥምረቱ መነሻውን ከሁሉም ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከተቋቋሙ የሸማች መብት ጥበቃ ማህበራት ያደረገ ነው ተብሏል።


የክልሎቹን እና የከተማ አስተዳደሮቹን ስብጥር ያካተተ የቦርድ አባላትም ተሰይመውለታል።


ጥምረቱ ሸማቾች በህግ የተሰጧችውን መብቶች እንዲያውቁ እና በግብይት ሂደት የሚገጥሙ የመብት ጥሰቶች እንዲስተካከሉ ይሰራል ሲሉ፤ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ተናግረዋል።


በዚህም ሰፊውን የህብረተሰብ ክፍል ያቀፈው ሸማች መብት እንዲከበር ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።


በሚኒስቴሩ የሀገር ውስጥ የንግድና ሸማቾች ጥብቃ መሪ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መስከረም ባህሩ በበኩላቸው፤ ጥምረቱ ህብረተሰቡ ድረስ መዋቅር ያለው እንደሆነ ተናግረው፤ ተገቢ ባልሆነ መልኩ የዋጋ ተመን ለምርቶች እና አገልግሎቶች ሲወጣም አቋም እስከመያዝ ይሄዳል ብለዋል።


የጥምረቱ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ እንግዳ አስፋው ደግሞ የተሳሳቱት እንዲታረሙ ከማድረግ ባሻገር፤ መልካም የሚሰሩ ነጋዴዎችንም የማበረታታት ስራ እንሰራለን ብለዋል።


በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስተባባሪነት ለቀናት ሲከበር የቆየው የሸማቾች ቀን የማጠቃለያ መርሃ ግብርም በዚሁ ወቅት ተከናውኗል።


ንጋቱ ረጋሣ




የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Kommentare


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page