እጅ ያጠራቸውን አካል ጉዳተኞች ለመርዳት ከ 57 ዓመት በፊት የተቋቋመው ‘’የሀገር ጥበብ ማደራጃ ድርጅት’’ በሶስት ቀን ገደብ ብቻ ከመንግስት የተሰጠኝ መስሪያና መተዳደሪያ ቦታ ፈረሰብኝ አለ፡፡
ቦታው የሚገኝበት የካ ክፍለ ከተማ በበኩሉ ‘’ቦታው የፈረሰው ተነጋግረን ተግባብተን ነው’’ ብሏል፡፡
167 ሰራቶኞችን በስሩ የያዘው ይህ ድርጅት አካል ጉዳተኞች፤ ራሳቸዉ በሚሰሩት የተለያዩ የእጅ ጥበብ የሚያገኙት ገቢ አነስተኛ በመሆኑ በመንግስት ድጎማ ተደርጎላቸው ይተዳደሩ እንደነበር ተነግሯል፡፡
ነገር ግን የድጎማ በጀቱ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ በመምጣቱ፤ ድርጅቱ የተሰጠዉ ቦታ ላይ ሌላ ባዶ መሬት በመኖሩ ‘’ይህንን ቦታ አከራይተን እንጠቀም’’ የሚል ከድርጅቱ ሰራተኞች ጥያቄ ይቀርባል፡፡
በ1993 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ችግሩን በማየት ከመንግስት ይሰጥ የነበረዉን የድጎማ በጀት ሙሉ ለሙሉ ቀርቶ ቦታዉ ላይ ቤት ገንብተዉና አከራይተዉ እንዲጠቀሙ ይፈቅድላቸዋል፡፡
የሀገር ጥበብ ማደራጃ ድርጅት ይህንን ዉሳኔ ተቀብሎ ሱቆችን፣ መጋዘኖችን እና አዳራሾችን ገንብቶ በማከራየት እስካሁን ድረስ ለሰራተኞቹ ደሞዝ 80 በመቶ የሚሆነዉን ከዚሁ ተቀብሎ እንደሚከፍል ሰምተናል፡፡
አሁን ላይ ይህ ድርጅት ‘’እነዚህ የገነባኋቸዉ ቤቶች የመንገድ ኮሪደር በሚል በመፍረሳቸዉ ለከፋ ችግር ተጋልጫለሁ’’ ሲል ለሸገር ተናግሯል፡፡
እነዚህ አካል ጉዳተኞች ‘’እኛ ልማቱን እየተቃወምን ሳይሆን ልማቱ እኛን ያማከለ አይደለም፤ ጥያቄያችን የእንጀራ እና ዳቦ ብቻ ሳይሆን የህልዉና ጉዳይ ነዉ’’ ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክፍለ ከተማ በበኩሉ ‘’ቀድሞዉኑም ቦታዉ የመንግስት በመሆኑ ቦታዉ እንዲፈርስ ተደርጓል፤ ሆኖም ግን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments