አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስለ ኒውኩለር ቴክኖሎጂን ለማስተማር የሚያገለግል ላብራቶሪ ገንብቶ መጨረሱን ተናግሯል፡፡
ነገር ግን ላብራቶሪውን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ግብዓት አለማግኘቱን የተናገረ ሲሆን ይህንን ክፍተት ለመሙላት ከመንግስትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር እየሞከረ መሆኑን ሰምተናል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ጌታቸው አዳሙ ዩኒቨርሲቲው በኒውኩለር ቴክኖሎጂ ተማሪዎችን በ2ኛ ዲግሪ ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል ብለዋል፡፡
ከመጀመሪያ ዲግሪ አንስቶ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ነገር ግን የላብራቶሪ ጉዳይ አሳሳቢ ነው በማለት ነግረውናል፡፡
ዩኒቨርስቲው ከኮርያ ቻይና እና ከሩሲያ ጋር በኒውኩለር ቴክኖሎጂ ( #Nuclear_Technology ) ዙሪያ አብሮ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምር እና ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ጌታቸው አዳሙ አስረድተዋል፡፡

ከሀገራቱ ጋር በጋራ ጆይንት ፕሮግራም ከፍተን ተማሪዎች የንድፈ ሀሳብ ትምህርት እዚሁ እንዲማሩ የተግባሩ ደግሞ በሃገራቱ እንዲማሩ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comentarios