በምያንማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 32 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
በምያንማር በሚገኙ የሳይበር ወንጀል ካምፖች በግዳጅ ሠራተኝነት ተይዘው የነበሩ 138 ኢትዮጵያውያን ተለቅቀው ወደ ታይላንድ መግባታቸውን ከ15 ቀናት በፊት ተዘግቦ ነበር፡፡

ሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በምያንማር በእገታ ሥር ቆይተው ወደ ታይላንድ ከተሻገሩ 133 ኢትዮጵያ መካከል 32ቱ ዛሬ ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
43ቱ ደግሞ ዛሬ ምሽት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቀሪዎቹ በታይላንድ ማቆያ የሚገኙ 58 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ኤምባሲው ጥረት እያደረገ ይገኛል ተብሏል።
በተያያዘ መንግሥት ጃፓን በሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በምያንማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ወደ ታይላንድ በማሻገር ወደ አገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ ይገኛል ሲል መኒስቴር መ/ቤቱ አስረድቷል።
በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሀሰተኛ ቅስቀሳ ተታሎ የሥራ ስምሪት ውል ወዳልተፈጸመባቸው አገራት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንድትቆጠቡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።
በደቡብ ምሥራቅ እስያዋ ምያንማር ብዛት ያላቸው የሳይበር (የበይነ መረብ) ማጭበርበር የሚከናወንባቸው ካምፖች የሚገኙባት ሀገር ስትሆን "የሥራ ዕድል ታገኛላችሁ" በሚል ተታልለው በግዳጅ ለዚህ ድርጊት የሚዳረጉ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ያሉ ሲሆን ከእዚህ መካካል ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ይገኙበታል።
Comments