top of page

መስከረም 9 2018 - የሕፃን እና የወላጅ ትስስርን የሚቆጣጠር የነርቭ ዘዴን ሳይንቲስቶች ማገኘታቸው ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Sep 19, 2025
  • 1 min read

የእስራኤል ተመራማሪዎች ኦክሲቶሲን የተባለ የአንጎል ኬሚካል ህፃናት ከወላጆቻቸው የሚለዩበትን ሁኔታ እንዲቋቋሙ እንደሚረዳቸው አረጋግጠናል አሉ።


ግኝቱ በህጻናት እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ያሳያል ሲል ዌይዝማን የሳይንስ ተቋም ተናግሯል ። ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ የኦክሲቶሲን እንቅስቃሴ ህጻናት ከእናታቸው ሲለዩ በአእምሮ ውስጥ ተጽዕኖ እንደሚያደርስ አረጋግጠናል ብለዋል።


ኦክሲቶሲን ብዙ ጊዜ "የፍቅር ሆርሞን" ተብሎ ይጠራል። ምክንያቱም ማህበራዊ ትስስርን ለመፍጠር ስለሚረዳ ተብሏል። አዲሱ ጥናት እንደሚያሳየው ኦክሲቶሲን ከሰው ልጅ ባሻገር ገና በተወለዱ እንስሳት ስሜታዊ ባህሪ ላይም ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ነው።


በጥናቱ ወቅት የኦክሲቶሲን ስርዓት ያላቸው ጨቅላ ህጻናት ከእናታቸው በሚለያዩበት ጊዜ አምርረው ያለቀሱ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ የኦክሲቶሲን ስርዓት የሌላቸው በቀላሉ መላመዳቸውን አስረድተዋል ።


ኦክሲቶሲን ህጻናት ከእናታቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ የሚያሳዩት ባህሪ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ጥናቱ አሳይቷል።

የተመራማሪዎች ቡድን በሴቶች እና በወንዶች መካከል ልዩነቶችን ማግኘታቸውን ጠቁመው ሴት ህጻናት በኦክሲቶሲን እንቅስቃሴ ላይ በተደረጉ ለውጦች የበለጠ መጎዳታቸውን አረጋግጠዋል። ይህም ስሜታዊ እድገት ቀደም ሲል ከታሰበው በላይ በጾታ መካከል ልዩነት ሊፈጥር እንደሚችል ይጠቁማል ብለዋል።


ጥናቱ ከዚህ ቀደም ባሉ የህይወት ተሞክሮዎች ፣ የአዕምሮ ስርዓትን እና ማህበራዊ ባህሪን እንዴት እንደሚቀርጹ አዲስ ግንዛቤ እንደሚሰጥ ተመራማሪዎቹ ጠቁመዋል።


እንደ ኦቲዝም ባሉ ሁኔታዎች ላይ ለወደፊቱ ምርምር ፍንጭ ሊሰጥ እንደሚችል ገልጸዋል ሲል የቻይናው ሚዲያ ሺኑዋ ዘግቧል።


ትዕግሥት ፍሰሃ





Recent Posts

See All
የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡

ጥር 12/2018 የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር "ስራቸውን በአግባቡ አልሰሩም፣ ህግን አላከበሩም ፣ ኦዲት ሪፖርት ለዓመታት አላቀረቡም ፣ጠቅላላ ጉባዔም ወቅቱን ጠብቀው ማካሄድ አልቻሉም"በሚል ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡ የቀድሞ ቦርድ አባላት ስራቸወን በአግባቡ ባለመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page