መስከረም 9 2018 - በመጪው የበጋ የአየር ጠባይ በተለይ በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል ከፍተኛ የወባ ወረርሽኝ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡
- sheger1021fm
- Sep 19, 2025
- 1 min read
ይሄን ያለው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ነው፡፡
ባሳለፍነው የክረምት ወቅት የወባ በሽታ እና የኮሌራ ወረርሽኝ ተከስቶ እንደነበርም ሰምተናል፡፡
በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የጤና ሚቲዎሮሎጂ ባለመሞያው አቶ ደሳለኝ ታረቀኝ ባሳለፍነው የክረምት ወቅት በነበረው የአየር ጠባይ በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የወባ እና የኮሌራ ወረርሽኝ ተከስቶ ነበር ብለዋል፡፡
ወረርሽኙም በሰው ላይ ጉዳይ የሚያደርስ እንደነበር የነገሩን ባለሞያው የጉዳት መጠኑ በተመለከተ ግን መረጃው እንደሌላቸው ነግረውናል፡፡
አያይዘውም በመጪው የበጋ ወራት የሚኖረው የአየር ሁኔታ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ላይ የወባ ወረርሽኝ ይከሰታል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከዚህ ቀደም የወባ ወረርሽኝ ተከስቶ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ደሳለኝ አሁንም በበጋው ወራት በአካባቢው ወረርሽኝ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments