top of page

መስከረም 9፣2017 - ''የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎችን ለመቆጣጠር አስመጭዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረግኩ ነው'' የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

  • sheger1021fm
  • Sep 19, 2024
  • 1 min read

የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎችን ለመቆጣጠር አስመጭዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረግኩ ነው ሲል የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተናገረ።


ከዚህ ቀደም የኤሌክትሮኒክስ አስመጪዎች፤ ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ በሚያስገቡበት ሰዓት ምን እና ምን ያህል በሚለው ላይ በቂ የቁጥጥር ሥርዓት ባለመኖሩ ከፍተኛ የቆሻሻ ክምችት እንዲኖር ምክንያት መሆኑም ተነግሯል።


በኢትዮጵያ ካለው የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ ክምችት ቀዳሚውን የሚይዘው በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ እንደሆነም ሰምተናል።


ዘወትር የምንጠቀምባቸው እንደ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥንና መሰል የኤሌክትሮኒክ እቃዎች አገልግሎት ሲያቆሙ የአወጋገዳቸው ነገር ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡


እንዲሁ መሬት ላይ የሚጣሉ ከሆነ አፈርና ውሃን ለመበከል ከሰውና ለእንስሳት ጤና ጠንቅ የሚሆኑ የኤሌክትሮኒክ ቆሻሻዎችን በአግባቡ ለማስወገድ የአሰራር ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጓል ተብሏል፡፡


ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መጠን ለማወቅና አገልግሎታቸውን የጨረሱ ኤሌክትሮኒክስ በአካባቢው ተከማችተው ብክለት እንዳያስከትሉ አስመጭዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የማድረግ የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ እየተሰራበት ነውም ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህን ይጫኑ…


ፍቅሩ አምባቸው

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page