ከ14 ዓመታት በላይ ንግግር ሲደረግበት የቆየው የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ አለም አቀፍ ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ የሚያስችለውን ድምፅ ከወር በፊት ከደቡብ ሲዳን ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ በሀገራት መፈረም የጀመረው ከ14 ዓመት በፊት ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ፈራሚ ሀገራትም ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ነበሩ፡፡
በህግ አውጭ አካሎቻቸውም አፀድቀውታል፡፡
ብሩንዲም ኋላ ላይ እነ ኢትዮጵያን ተቀላቅላለች፡፡
የውሃ ምህንድስና ባለሞያው ጥሩ ሰው አሰፋ(ዶ/ር)፤ 6ኛ ሀገር ስምምነቱን ባጸደቀች በ60 ቀኑ የናይል ተፋሰስ የትብብር ኮሚሽን የሚባለው እውን ይሆናል ብለዋል፡፡
የሚቋቋመው የናይል ተፋሰስ የትብብር ኮሚሽን ቀዳሚ ስራው ምንድነው?
እንዴት ይሰራል? ገንዘብስ ከየት ያመጣል?
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ…
ንጋቱ ሙሉ
ተያያዥ ዘገባዎችን ያድምጡ …
Comments