top of page

መስከረም 9፣2017 - ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የንግድ ስራ አብዛኛው የቤተሰብ ቢዝነስ እንደመሆኑ ከትውልድ ትውልድ ውጤታማ ሆኖ እንዲሸጋገር፣ የማስተማር ስራ እየከወነ መሆኑን HST የተሰኘ ድርጅት ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Sep 19, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የንግድ ስራ አብዛኛው የቤተሰብ ቢዝነስ እንደመሆኑ ከትውልድ ትውልድ ውጤታማ ሆኖ እንዲሸጋገር፣ የማስተማር ስራ እየከወነ መሆኑን ኤችኤስቲ(HST) የተሰኘው አማካሪ ድርጅት ተናገረ፡፡


የቢዝነስ አስተዳደር እና ፋይናንስ አማካሪ ተቋም የሆነው የHST ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ግዛው እንዳሉት በአብዛኛው የቤተሰብ ንግድ እውቀት ባለው ባለሞያ እንዲመራ ስለማይደረግ የመዳከም እና የመክሰም ችግር ያጋጥመዋል፡፡


ይህንንም በመረዳት ቤተሰባዊ የሆነው የንግድ ስራው ቀጣይነትን ያለውና ውጤማ እንዲሆንም የማማከርና የማስተማር ስራ እየከወንን ነው ይላሉ፡፡


የቤተሰብ ቢዝነስ መክሰምም ለሃገር ኢኮኖሚ ጭምር ጫና ስለሚፈጥር እንዲበረታ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡


ተቋማቻው በየአመቱ የቤተሰብ ንግድን በተመለከተ ግንዛቤ ለመስጠት የሚያስችል ውይይት እንደሚያዘጋጀ ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡


ትናንትም ይሄንኑ የተመለከተ ውይይት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ማድጉን ነግረውናል፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ንግድ የቤተሰብ መሆኑንም ጠቅሰው ነገር ግን አብዛኞቹ ማደግ የማይችሉት በዚህ ምክንያት ነው ይላሉ፡፡


የቤተሰብ ንግዶች እውቀት ባለው ሰው እንዲመሩ ከተደረገና ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላኛው ውጤታማ ሆነው መሻገር ከቻሉ የሚፈጥሩት ሀብት እና የስራ እድል የሃገር ኢኮኖሚም ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡




Commenti


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page