15 አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁም እንድታደርግ ጫና እንዲደረግባት ጠየቁ፡፡
በእስራኤል ላይ አለም አቀፍ ጫና እንዲበረታባት ከጠየቁት አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች መካከል ኦክስፋም፣ ሴቭ ዘ ቺልድረን እና ክርስቲያን ኤድ የተወሰኑት እንደሆኑ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡
የረድኤት ድርጅቶቹ የጋዛውን ጦርነት ለማስቆም በእስራኤል ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብም እንዲደረግባት ጠይቀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በጦርነቱ ምክንያት ወደ ጋዛ መድረስ የነበረበት 85 በመቶ እርዳታ መስተጓጎሉ ተጠቅሷል፡፡
ከጦርነቱ በፊት በየቀኑ 500 የጭነት መኪና እርዳታ ሲገባ ቆይቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት ግን በየእለቱ የሚገባው ሰብአዊ እርዳታ ከ69 የጭነት መኪና አይበልጥም ተብሏል፡፡
Comments