የአማራ ክልል የሰላም ምክር ቤት ‘’ጠቅላይ ሚኒስትሩን አግኝቼ ካላወራኋቸው የተሰጠኝ ሃላፊነት ውጤት ላያመጣ ይችላል’’ ሲል ተናገረ፡፡
መንግስትን እና የፋኖ ሃይሎችን ለማደራደር የማመቻቸት ድርሻ ወስዶ የተቋቋመው የአማራ ክልል የሰላም ምክር ቤት ‘’ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን አግኝቼ በክልሉ ስላለው ሁኔታ መምከር እፈላጋለሁ’’ ብሏል፡፡
ለዚህም ‘’ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያነጋገሩን ጠይቀናል’’ ያሉን የሰላም ምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ ናቸው፡፡
አቶ እያቸው የአማራ ክልል ችግር እዛው የክልሉ ሰዎች እንደፈላጋችሁ አድርጉት የሚባል አይደለም ምክንያቱም ከክልሉ ወጣ ያሉ በርካታ አውዶች አሉት ብለዋል፡፡
በአማራ ክልል ያለው ግጭት ከክልሉ አለመውጣቱ ሳይሆን መታየት ያለበት ምክንያቱ ነው ሲሉ ኃላፊው ተናግራዋል፡፡
የክልሉ ህዝብ ብዛት እና የቆዳ ስፋት ምን ያህል እንደሆነ ይታወቃል እንዲሁ ዝም ብሎ በሚድያ አልያም በመድረክ ላይ ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ማለት ብቻውን በቂ አይደለም ሲሉ አቶ እያቸው ነግረውናል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩን አግኝተን ካነጋገርናቸው እስካሁን የድርድር ፍላጎቱ ያለው ከክልሉ መንግስት ብቻ ነው ያለው የሚባለውን ሃሜት የሚያስቀር ከፌዴራል መንግስት በኩልም ፍላጎት መኖሩንም ማረጋገጫ ይሆናል ብለዋል አቶ እያቸው፡፡
ከፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው መመካከራችን በመንግስት እና በፋኖ ብቻ ሳይሆን በምክር ቤቱ እና በመንግስት መካከል መተማመን ይፈጥራል ብለዋል የሰላም ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ፡፡
ይህም የምናቀርባቸው ሃሳቦች ተቀባይነት እንዲኖራቸው ይረዳል ብለዋል፡፡
ሁሉን ነገር በቅርበት ተማምነን መስራት ካቻልን ውጤት ላያመጣ ይችላል ዝም ብሎ የሰላም ምክር ቤት አቋቁሚያለሁ ማለትም ፋይዳ የለውም ሲሉ አቶ እያቸው ተሻለ አስረድተዋል፡፡
የሰላም ምክር ቤቱ እስካሁን ከአሜሪካ ኤምባሲ፣ ከኢጋድ፣ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከክልሉ ፕሬዝዳንት እና ከሌሎችም ጋር መከሪያለው ብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ
ያሬድ እንዳሻው
Comments