top of page

መስከረም 8፣2017 - የኢጋድ የ10 ዓመት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን አባል ሀገራት በጋራ መሰረተ ልማት እንዲያለሙ ያግዛል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Sep 18, 2024
  • 1 min read

የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት(IGAD) የ10 ዓመት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን አባል ሀገራት በጋራ መሰረተ ልማት እንዲያለሙ ያግዛል ተባለ።


የኢጋድ(IGAD) አባል ሀገራት የበለጠ ከዘርፉ ለመጠቀም ከፈለጉ #የቪዛ_አገልግሎታቸውን ወጥ እንዲሆን ኢጋድ ፍላጎት አለው ተብሏል።


የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ በኢጋድ አባል ሀገራት የእርስ በእርስ የቱሪስቶች ጉብኝት ዝቅተኛ ነው ብለዋል።


የውጪ ሀገራት ጎብኚዎችም ቢሆን ቀጠናው ካለው የቱሪዝም ሃብት ጋር ሲተያይ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።


ይህም የሆነው የአባል ሀገራት የእርስ በእርስ #የቱሪዝም_መረጃ ዝቅተኛ መሆን፣ የመሰረተ ልማት ጥራት አነስተኛ መሆንና የጋራ ቪዛ አገልግሎት አለመጠቀም ተጠቃሽ ናቸው።


አሁን ኢጋድ ያዘጋጀው ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን እነዚህ ችግሮች ከመፍታት ባለፈም ቀጠናው የተሻለ የቱሪዝም ፍሰት እንዲኖረው ያደርጋል ተብሏል።


ይህ እውን እንዲሆን በቀጠናው በየጊዜው የሚነሳው #ግጭትና የሰላም እጦትም ችግር ሊፈታ ይገባልም ተብሏል።

የቱሪዝም ሚንስትሯ ናሲሴ ጫሊ የ10 ዓመቱ የኢጋድ ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን በአባል ሀገራት መካከል የጋራ የእርስ በእርስ ግንኙነት ያሳድጋል፤ በተለይም ቀጠናው ያለው የቱሪዝም ሀብት በጋራ አልምቶ ለመጠቀምና የተሻለ መሰረተ ልማት ለመገንባት ይረዳል ሲሉ ተናግረዋል።


የአፍሪካ የእርስ በእርስ የቱሪዝም ፍሰት 12 ከመቶ ብቻ ሲሆን ይህንን ወደፊት ማሻሻልና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶችን ቁጥር ማሳደግ ይገባል ለዚህ ደግሞ በሀገራቱ መካከል መረጃ መለዋወጥ ያስፈልጋል ተብሏል።


የኢጋድ አባል ሀገራት የቱሪዝም ሚንስትሮች ስብሰባ ኢትዮጵያ እያስተናገዳች ሲሆን መስከረም 9 የኢጋድ የቱሪዝም ማስተር ፕላን ላይ ይፋ ይደረጋል።


በረከት አካሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page