top of page

መስከረም 8፣2017 - በዋግህምራ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ 29 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል

ባለፉት 3 ዓመታት ዝናብ ጠብ ባለማለቱ በድርቅ ሲፈተን የቆየው የዋግህምራ ዞን በ2016 የክረምት ወቅት ዝናብ ቢያገኝም በአንዳንድ የዞኑ አካባቢዎች ከፍተኛ ዝናብ በማጋጠሙ ምክንያት ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል ተባለ፡፡


በዞኑ አንዳንድ ወረዳዎች ከፍተኛ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ ጎርፍ እንደተከሰተ የተነገረ ሲሆን በመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ 29 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም በደራሽ ጎርፍ ከ400 በላይ እንሰሳት ሲሞቱ 195 የሚሆኑ የአርሷ አደር ቤቶች በላያቸው ላይ መፍረሱን ሸገር ራዲዮ ሰምቷል፡፡


ሸገር ይህንን የሰማው ከዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ነው፡፡


ነሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በዞኑ የጀመረው የዝናብ ወቅት ከሀምሌ 11 ቀን ጀምሮ ግን ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ መዝነብ እንደጀመረ የተናሩት የፀህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ምህረት መላኩ የመሬት መንሸራተት፣ ጎርፍ እና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ አስተናግደናል ብለዋል፡፡


በተጨማሪም በርከት ያለ ሄክታር ላይ የበቀሉ ሰብሎች ላይ ጉዳት ማድረሱን የተናገሩት ሀላፊው ከ6,000 ሄክታር በላይ መሬት እና ሰብል ከጥቅም ውጭ ሆኗል ብለዋል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page