top of page

መስከረም 7፣2017 - ጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።


ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።


"ከልብ አዝኛለሁ" ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

''በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ'' ሲሉም ፕሮፌሰር በየነን ገልፀዋቸዋል።


ፕሮፌሰር በየነ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡


ኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ(ኢሶዴፓ) ሊቀመንበርም ነበሩ፡

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page