መስከረም 8፣2017 - ዘመን ባንክ ከምስረታው ጀምሮ አብረውት የሰሩትን ደንበኞቹን አመሰገነ
- sheger1021fm
- Sep 18, 2024
- 1 min read
ዘመን ባንክ ከምስረታው ጀምሮ አብረውት የሰሩትን ደንበኞቹን አመሰገነ፣ እውቅናም ሰጠ።
የዘመን በንክ የደንበኞች እና አጋሮች የምስጋና እና እውቅና ፕሮግራም የተካሄደው በሸራተን ሆቴል በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ነው።
ከ200 በላይ ከባንኩ ጋር ሲሰሩ የቆዩ ደንበኞች እና አጋሮች ሰርተፍኬት እና ስዕል ተበርክቶላቸዋል።
በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በአበባ እርሻ ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአየር ትራንስፖርት፣ በሆቴል እና ቱሪዝም የሰሩ እንዲሁም አብረውት ለሚሰሩ ዓለም- አቀፍ ድርጅቶች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ዕውቅና ሰጥቷቸዋል።
የዘመን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ዘበነ
"ዛሬ የባንኩን ያላፉት 16 ዓመታት የስኬት ጉዞ ስናወድስ ያለ እናንተ ቁርጠኛ ድጋፍ የስኬት ታሪክችን ጎዶሎ እንደሆነ ላረጋግጠላችሁ እወዳለሁ፤ እገዛቸሁ እና አብሮነታቸሁ ለእኛ ዓለማችን ነው፤ ስለዚህም የጉዛችን ድንቅ እካል በመሆናቸሁ እናመሰግናችሁለን"ሲሉ ደንበኞቻቸውና አጋሮቻቸውን አመስግነዋል፡፡

የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እነዬ ቢምር "ከእናንተ ጋር በመስራታችን፤ እናንተን በማገልገላችን እንኮራለን፤ ለብዙዎች የስራ እድል የፈጠራችሁ፤ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ግንባታ በተለያየ መንገድ አስተዋጽኦ እያደረጋችሁ ካላችሁ ከእናንተ ጋር አጋሮች በመሆናችን እጅግ ደስተኞች ነን" ሲሉ የባንኩን ደንበኞች እና አጋሮች አመስግነዋል።
የኢትዮጰያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኩ ላደረገው ያልተቋረጠ ክትትልና ድጋፍ የቦርድ ሰብሰባዊ አመስግነዋል።
2001 ዓ. ም ስራ የጀመረው ዘመን ባንክ በአሁኑ ሰዓት በ127 ቅርንጫፎች፣ በ293 ኤቲኤሞች እና በ801 ፖስ ማሽኖች በመታገዝ ደንበኞቹን እያገለገለ ይገኛል ሲሉም ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል፡፡
የባንኩ የተፈረመ ከፒታል 15 ቢሊዮን ብር፣ የተከፈል ከፒታሉ ደግሞ 7.5 ቢሊዮን ብር እና ህጋዊ መጠባበቂያው 1.7 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተነግሯል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments