top of page

መስከረም 6፣2017 - የግብርና ሚኒስቴር በተጠናቀቀው 2016 ዓ.ም እሰራዋለሁ ካለው ጉዳይ አንዱ አሲዳማ መሬትን ማከም ነበር

ኢትዮጵያ ከምታርሰው መሬት ውስጥ 43 ከመቶ ወይም 7 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው መሬቷ በአሲድ እንደተጠቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተናግሮ ነበር፡፡


ከዚህ ውስጥ 3.1 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው በጠንካራ አሲዳማነት የተጠቂ አፈር ነው፡፡


መሬቱን ለግብርና ስራ ለማዋል በዓመት 6.2 ሚልየን ኩንታል ማዳበሪያ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን መሬቱ አሲዳማ በመሆኑና በአግባቡ ስለማይቀበለው 70 ከመቶ የሚሆነው የአፈር ማዳበሪያ ይባክናል ተብሏል።


በዚህም ሀገሪቱ 19 ቢሊዮን ብር በአፈር አሲድ ምክንያት በዓመት ይባክንባታል ሲል የግብርና ሚኒስቴር ተናግሯል።


የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ በ #አሲዳማ_አፈር ምክንያት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ምርት ይባክንባታል ሲሉም አስረድተዋል።


አሲዳማ አፈር በአብዛኛው የሚከሰተው በደጋ እና ወይና ደጋ የኢትዮጵያ ክፍል አካባቢ ነው ያሉት ሚንስትሩ ለዚህም ምክንያቱ መሬቱ፤ በዝናብ ስለሚታጠብና በአንዳንድ የአፈር ማዳበርያ አጠቃቀም ተብሏል፡፡

አሲዳማ አፈር ኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል የሚሉት ያለው የግብርና ሚንስቴር ይህንን ከወዲሁ ለማከም ኖራ እየተጠቀመ ይገኛል።


በዚህ ምክንት #የግብርና_ሚኒስቴር በክረምት ወቅት የመህር እርሻው ሲካሄድ ጎን ለጎን ቢያንስ 50,000 ሄክታር መሬት ሰርቶ ማሳያ አሲዳማ መሬትን ለማከም እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነበር፡፡


ይህንን በተመለከተ ከምን ደረሰ ብለን በግብርና ሚኒስቴር በተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ የአፈር ሀብት ልማት ስራ አስፈፃሚውን አቶ ሊሬ አብዩን ጠይቀናቸዋል፡፡


አቶ ሊሬ በዚህ ወቅት ለመስራት ከታቀደው የአሲዳማ አፈር የማከም ስራ የተሳካው 15,000 ሄክታር የሚጠጋ መሬት ብቻ ነው ብለዋል፡፡


ለምን የታቀደው እቅድ አልተሳካም ብለን አቶ ሊሬን ጠይቀናቸዋል፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታረሰው መሬት ከአሲዳማነት ባለፈ ሌሎችም ምርትና ምርታማነት እንዲቀንስ የሚያደርጉ እንደ ጨዋማ መሬትና ሌሎች በግብርናው ዘርፍ አሁን ላይ ያሉ ችግሮች እንደሚስተዋል ያስረዳሉ፡፡


አሁን ማሳካት ያልተቻለው አሲዳማ አፈር የማከም ስራ በ2017 ላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎች በአማራጭነት በመጠቀም እቅዱን ለማካካስና የበለጠ ለመስራት ውጥን አለን ሲሉ አቶ ሊሬ ያስረዳሉ፡፡


በበጋ ወቅት በሚካሄዱ የግብርና ስራዎች ጎን ለጎን የግብርና ኖራ ምርት እንዲጨምር በማድረግ ከአሁን በተሻለ መንገድ በመስራት አሲዳማ አፈር ማከም አለብን ይህ ከሆነ ምርትና ምርታማነት ያድጋል ሲሉ ነግረውናል፡፡



በረከት አካሉ

Comentários


bottom of page