top of page

መስከረም 6፣2017 - ኢትዮጵያ የውጪ አልሚዎች በአይሲቲ(ICT) የስራ መስክ ኢንዲሳተፉ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ አይሲቲ ፓርክ ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Sep 16, 2024
  • 1 min read

በተያዘው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ የውጪ አልሚዎች በአይሲቲ(ICT) የስራ መስክ ኢንዲሳተፉ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ አይሲቲ ፓርክ ተናገረ፡፡


አሁን ባለው የICT ፓርክ ህንፃ ሁሉም ቦታዎች በሀገር ውስጥ አልሚዎች ተይዘዋል ያሉት የፓርኩ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሄኖክ አህመድ ናቸው፡፡


ስራ አስኪያጁ በገባው አዲስ ዓመት ለውጪ አልሚዎች የሚሆኑ የስራ ቦታዎችን እናሰናዳለን ብለዋል፡፡


በዚህም የውጪ አልሚዎች በICT መስክ እንዲሳተፉ ይደረጋል ሲሉ አቶ ሄኖክ ነግረውናል፡፡


አሁን ላይ 32 የሀገር ውስጥ አልሚዎች በፓርኩ የሥራ ቦታ ተከራይተው እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page