ፀሐይ ባንክ የጀመረው የክሬዲት ካርድ አገልግሎት ከተለመደው የዴቢት ካርድ የሚለየው ደንበኞች በተፈቀደላቸው የብድር መጠን የብድር ዘመኑ እስከሚያበቃ ድረስ እንደፈለጉ መጠቀም የሚችሉ ሲሆን፤ ይህም ደንበኞች ለሚገጥማቸው ጊዜያዊ ወይም አስቸኳይ የገንዘብ ችግር ትልቅ መፍትሄ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡
ደንበኞች የክሬዲት ካርዱን ለመጠቀም ምንም አይነት ማስያዣ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም ሲባልም ሰምተናል።
የሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያም እጅግ ተመጣጣኝና በተጠቀሙት የገንዘብ መጠን ልክ ብቻ ይሆናል ሲሉ የባንኩ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ያሬድ ተናግረዋል፡፡
ፀሐይ ባንክን ይህንን አገልግሎት መስጠት የጀመረው ከባንኩ ጋር የስራ ግንኙነት ላላቸው ተቋማት ሰራተኞች እና የባንኩ ቀዳሚ ደንበኞች ሲሆን፣ አግልግሎቱ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞችን ያካትታል ተብሏል።
የክሬዲት ካርድ አገልግሎቱ ደንበኞች የሚገጥማቸውን ጊዜያዊ የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ ያግዛል፣ከባንኩ በብድር የሚያገኙትን ገንዘብ በካርድ ጠቀም ያስችላቸዋል፣ለግብይት የሚያስፈልጋችውን ገንዘብ ወዲያው ተጠቅመው ቆይተው እንዲከፍሉ ያስችላቸዋል ተብሏል።
የፀሐይ ባንክ የክሬዲት ካርድ አገልግሎት ከባንክ ብድር ማግኘት ላልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመድረስ ከፍተኛ አቅም ይፈጥራል ሲሉ ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የክሬዲት ካርድ ተጠቃሚ ደንበኞች ብድር ታሪክ መመስረትና መሰነድ የሚያስችላቸው ሲሆን ወደፊት ለሚኖራቸው ማንኛውም ዓይነት የብድር አገልግሎት ጥያቄ ትልቅ ውሳኔ መረጃ ግብዓት በመሆን እንደሚያገለግል ታምኖበታል፡፡
ደንበኞች የወሰዱትን ብድር ተጠቅመው ሲመልሱ የብድር መጠናቸው እያደገ እንደሚሄድ ተነግሯል።
የክሬዲት ካርድ ብድር መመለሻ ጊዜው ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ሲሆን የደንበኞች መመለስ አቅምና ፍላት እየታየ አገልግሎቱ እንደሚራዘም አቶ ያሬድ አስረድተዋል።
የፀሐይ ባንክ ደንበኞች ሒሳብ ወደ ከፈቱበት ቅርንጫፍ በመሄድ የክሬዲት ካርድ ባለቤት መሆን ይችላሉ ተብሏል፡፡
ሓምሌ 16/2014 ስራ የጀመረው ፀሐይ ባንክ የቅርንጫፎቹ ብዛት 82፣ የደንበኞቹ ብዛት ደግሞ ከ280 ሺህ በላይ እንደደረሱለት ተናግሯል ።
የተከፈለ ካፒታሌ 1.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል ያለው ባንኩ አጠቃላይ ሀብቱ ደግሞ 3.5 ቢሊየን ብር እንደሆነ ሲነገር ሰምተናል።
ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz