top of page

መስከረም 30፣2017 - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የመማር ማስተማሩ አሁን እየታየ ያለው የሰላም እጦት ስራዬን እንዳያስተጓጉለው ያሰጋኛልም ብሏል

መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም እጦት ያሉባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎችን ጨምሮ ትምህርት ተጀምሯል፡፡


የሰላም እጦት ከነበሩባቸው እና አሁንም ድረስ ችግሩ ከቀጠሉባቸው አካባቢዎች መካከል አማራ ክልል አንዱ ነው፡፡


የመማር ማስተማሩ አሁን እየታየ ያለው #የሰላም_እጦት ስራዬን እንዳያስተጓጉለው ያሰጋኛልም ብሏል፡፡


በክልሉ ያሉ ትምህርት በቤቶችን በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት እንጥራለን የሚለው የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሰላም እጦቱ አሁን ስጋት በፈጠረብን ልክ የሚዘልቅ ከሆነ ግን የመማር ማስተማር ሂደቱ ችግር ያጋጥመዋል ብለዋል፡፡


የዚህ ሁሉ ችግር የሚንፀባረቀው ተማሪዎች ላይ ነው የሚሉት የክልሉ ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን የትምህርት አቀባበላቸው እንዲቀንስ ሴቶች ደግሞ ያለ እድሜ ጋብቻ እንዲጋለጡ ያደርጋል ይላሉ፡፡

በተጨማሪም ባሳለፍነው የትምህርት ዘመን በሰላም እጦት ምክንያት የ6ተኛ፣ የ8ተኛ እና የ12 ክፍል ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች ነበሩን ያሉት ሀላፊው በዘንድሮው አመት በሁለተኛ ዙር እንዲፈተኑ እናደርጋለን ብለዋል፡፡


በሌላ በኩል እንደ ሀገር በ2015 ዓ.ም ወደ ትግበራ የገባውን አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት የያዘውን መፀሀፍ ለተማሪዎች የማዳረሱን ስራ ከምን ደረሰ? ስንል የጠየቅናቸው #የአማራ_ክልል_ትምህርት_ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን በ2016 ዓ.ም ከ14 ሚሊየን በላይ የአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ እና 4.6 ሚሊየን ገደማ የሁለተኛ ደረጃ መፀሀፍትን አዳርሰናል ብለዋል፡፡


በተያያዘው በጀት አመት ደግሞ ክልሉ 1 ቢሊየን ብር በመመደብ የ #መፀሀፍት ህትመት እያከናወነ ነው ያሉት ሀላፊው ይህም ሆኖ ለተማሪዎች አንድ ለአንድ አይዳረስም ብለዋል፡፡


በትምህርት ዘርፉ ችግሮችን ሲያስተናግድ የቆየው የአማራ ክልል በተያዘው የትምህርት ዘመን 7 ሚሊየን ተማሪዎችን ለመቀበል አቅዶ ከነሀሴ ወር ጀምሮ እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ የተመዘገበው የተማሪ ቁጥር 2 ሚሊየን የሚጠጋ ብቻ ነው ተብሏል፡፡


ይህ ቁጥር የሚያሳየው አምና በትምህርት ላይ የነበሩ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ዘንድሮ ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ነው፡፡

አምና በክልሉ 7 ሚሊየን ተማሪ መመዝገብ ነበረበት ቢባል ትምህርት ላይ የነበሩት ትምህርት ላይ የነበሩት 5 ሚሊየን ብቻ እንደነበሩ የትምህርት ቢሮው መረጃ ያሳያል፡፡


ዘንድሮ ደግሞ ቁጥሩ ከዛም ቀንሶ የተመዝጋቢዎች ቁጥር 2 ሚሊየን ብቻ ሆኗል፡፡


ይህም አምና ትምህርት ላይ የነበሩ 3 ሚሊየን ተማሪዎች ዘንድሮ ወደ ትምህርት እንዳልተመለሱ ያሳያል፡፡


በአጠቃላይ ግን በክልሉ 5 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው፡፡


ሰሞኑን በክልሉ ባለው ጦርነት ምክንያት ባህር ዳርን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እየሄዱ እንዳልሆነ ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/2v8bxhja


ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


bottom of page