top of page

መስከረም 30፣2017 -ኦቪድ ሪል ስቴት ለሀይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ) አሽከርካሪዎች እና ከሰዋሰው ጋር ለሚሰሩ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች የመኖርያ ቤት ሊገነባ ነው

ኦቪድ ሪል ስቴት ለሀይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ) አሽከርካሪዎች እና ከሰዋሰው ጋር ለሚሰሩ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች የመኖርያ ቤት ሊገነባ ነው፡፡


ለራይድ አሽከርካሪዎች "የራይድ መንደር" በሚል በገላን ጉራ ከተማ "የራይድ ቤተሰብ መንደር" ን ለመገንባት በዛሬው ሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ኦቪድ ሪል ስቴት ተፈራርመዋል፡፡


በተመሳሳይ በ #ሰዋሰው_መልቲ_ሚዲያ ጋር ለሚሰሩ የጥበብ ባለሞያዎች፣ አርቲስቶች፣ ዲጄዎች እና ከያኒያንን በተመጣጣኝ ዋጋ እና በልዩ ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ቅናሽ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስምምነት ተደርጓል።


ኦቪድ ሪል ስቴት ከሁለቱ ተቋማት ጋር በገባው ስምምነት መሠረት 5,000 ቤቶችን በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሰርቶ እንደሚያስረክብ ተናግሯል።

ለሃይብሪድ ዲዛይንስ ( #ራይድ ) አሽከርካሪዎች በ10% ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ዕድል መመቻቸቱን፣ ምዝገባውም ዛሬ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በራይድ ቢሮዎች እንደሚደረግ የድርጅቱ መስራች እና ባለቤት ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ አስረድተዋል።


በስምምነታቸው መሰረት #ኦቪድ_ሪል_ስቴት ለራይድ ትራንስፖርት፣ በስሩ ለሚገኙ ተቋማት እና ራይድ ቤተሰብ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ የዋጋ ቅናሽ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን በአጠቃላይ በኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የራይድ መንደር ለመገንባት ተሰማምቷል።


ሀይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ) ደግሞ ለሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ለሚገኙ ደንበኞቹ ኦቪድ ሪል ስቴት ስለሚያቀርበው የቤት ሽያጭ አገልግሎት ገበያውን በማስተዋወቅ ይሰራል፣ ያስተባብራል ተብሏል፡፡

ከስዋሰው መልቲ ሚዲያ ጋር የሚሰሩ የጥበብ ባለሞያዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በልዩ ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ቅናሽ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት እድል ተመቻችቷል የተባለ ሲሆን ባለሞያዎቹም ኦቪድ ረል ስቴት የሚያቀርባቸውን የቤት ሸያጭ ከአጋሮቹ ጋር ያከናውናል ሲባል ሰምተናል፡፡


በዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለነዋሪዎች እያስረከበ የሚገኘው ኦቪድ ሪል ስቴት ከ70,000 በላይ ቤቶችን በተለያዩ ሳይቶች እየገነባ መሆኑን አስረድቷል፡፡


ከዚህ ውስጥም 60,000 የሚሆኑት በገላን ጎራ ከተማ እየተገነቡ ያሉ መሆናቸውን የኦቪድ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬው በየነ ጠቅሰዋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

תגובות


bottom of page