top of page

መስከረም 30፣2017 - ህሙማን የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ መንግስት ጤና ተቋማት ሲሄድ ስድብን ጭምሮ የተለያ ውክቢያዎች እንደሚደርስባቸው ተነገረ

ህሙማን የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ መንግስት ጤና ተቋማት ሲሄድ ስድብን ጭምሮ የተለያ ውክቢያዎች እንደሚደርስባቸው ተነገረ፡፡


ይህ የተነገረው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ላይ ባደረገው ወይይት ነው፡፡


የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ህሙማንን ከእንግልት እና ከማመነጫጨቅ የሚጠብቅ እንዲሆን ተጠይቋል፡፡


ነዋሪዎች የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ መንግስት የጤና ተቋማት ሲሄዱ ክብራቸውን በጠበቀ መንገድ እንዲስተናገዱ የእንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ጠይቀዋል፡፡


የጤና ተቋማት ህክምና እርዳት ሲሰጡ የታካሚውን ክብር እንዲጠብቁ በአዋጅ ሊካተት ይገባል ሲሉ የምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ አስቻለ አላምሬ ተናግረዋል፡፡


የጤና አገልግሎት የስነምግባር መርሆች ላይም ቅንነት እና ታማኝነት በረቂቅ አዋጁ እንዲካተት ተጠይቋል፡፡

ያሬድ እንዳሻው

댓글


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page