top of page

መስከረም 3፣2017 - ''ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚሰጧቸው የትምህርት ፕሮግራሞች እውቅና መስጠት እጀምራለሁ'' የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

2017 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚሰጧቸው የትምህርት ፕሮግራሞች እውቅና መስጠት እጀምራለሁ ሲል የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተናገረ።


ባለስልጣኑ ይህንን ያለው #አድማስ_ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው 16ተኛው አለም አቀፍ አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ ነው።


በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚነሳውን የትምህርት ጥራት መጓደል ለማስተካከል እየሰራ መሆኑን የተናገረው ባለስልጣኑ ተቋማትን እንደገና መዝግቦ በጥራት እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያግዝ #መመሪያ እና አሰራር ሲያወጣ ሁለት አመት ማስቆጠሩን ተናግሯል።


ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር በተመዘገቡበት የትምህርት ዘርፍ ማስተማር ይችላሉ ውይ የሚለው ብቻ ታይቶ ፈቃድ ይሰጣቸው እንደነበረ የተነገረ ሲሆን በአዲሱ የጥራት መመዘኛ መመሪያ መሰረት አስፈላጊውን የጥራት ደረጃ ማሟላታቸው እየተመዘነ ዳግም እንዲመዘገቡ ይደረጋል መባሉን ሰምተናል፡፡


#የትምህርት_ጥራትን ለማረጋገጥ ይረዳል የተባለው ይህ አሰራር ከመጭው የትምህርት ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ተገባራዊ ይሆናል የተባለ ሲሆን በሂደት የመንግስት ዩንቨርሲቲዎችም ምዝናው አይቀርላቸውም ተብሏል፡፡



ፋሲካ ሙሉወርቅ

Komentar


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page