top of page

መስከረም 29፣2017 - ''መንግስትንና የፋኖ ሃይሎችን ለንግግር እንዲቀመጡ ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ላይ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ አካላት አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድረውብኛል’’ የአማራ ክልል የሰላም ም/ቤት

የአማራ ክልል የሰላም ምክር ቤት ‘’ያልተረዱኝ’’ ያላቸው በተለይም ከኢትዮጵያ ውጭ ሆነው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ አካላት ‘’መንግስትን እና የፋኖ ሃይሎችን ለንግግር እንዲቀመጡ ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድረውብኛል’’ ሲል ተናግሯል፡፡


ከወራቶች በፊት መንግስትን እና የፋኖ ሃይሎችን ለድርድር እንዲያመቻች የተቋቋመው ምክር ቤቱ ‘’በየማህበራዊ ሚዲያው የመንግስት ጉዳይ ፈፃሚ ተደርጌ እየተሳልኩኝ ነው’’ ሲል ወቅሷል፡፡


የክልሉ የሰላም ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ ‘’በክልሉ እየተሰቃየ ላለው ህዝብ የሚበጀው ፋኖ እና መንግስት ተቀራርበው እንዲነጋገሩ መስራት ነው’’ ብለዋል፡፡


‘’የክልሉ የሰላም ምክር ቤት አሁን ብገልጸው ለሰላም ሂደቱ እንቅፋት ስለሚሆን እንጂ ሁለቱን አካላት ለማቀራረብ በማደርገው ጥረት ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈልኝ ነው’’ ብሏል፡፡




ቀደም ተብሎ የተሰራ ተያያዥ ዘገባን ለማድመጥ… https://tinyurl.com/4vss484f


ያሬድ እንዳሻው

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page