ሁለት ሳምንታት ባልሞላ ጊዜ ሩብ ሚሊዮን ሊባኖሳውያን ወደ ሶሪያ ተሰድደዋል ተባለ፡፡
ሊባኖሳውያን ወደ ሶሪያ መሰደድ የያዙት እስራኤል በአገሪቱ ላይ የምትወስደውን ወታደራዊ እርምጃ በማክፋቷ እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡
2 ሳምንታት ባልሞላ ጊዜ 250,000 ሊባኖሳውያን ወደ ሶሪያ መሰደዳቸው አረጋግጫለሁ ያለው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን(UNHCR) ነው፡፡
እስራኤል ሊባኖስ ውስጥ በፈፀመችው ጥቃት 1,251 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
ከ3,600 በላይ ደግሞ ለተለያየ ደረጃ አካላዊ ጉዳት ተዳርገዋል፡፡
መካከለኛው ምስራቅ ወደ ከፋ ቀጠናዊ ጦርነት ሊያመራ ይችላል የሚለው ስጋት አይሏል፡፡

አሜሪካ ባለፈው 1 ዓመት ለእስራኤል የ18 ቢሊዮን ዶላር ያህል የጦር ድጋፍ አድጋለች ተባለ፡፡
የአሜሪካ የጦር ድጋፍ ወጪ የተሰላው በብራውን ዩኒቨርሲቲ እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ መዘገቡን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡
እስራኤል የጋዛ የጦር ዘመቻዋን ከጀመረች ከአመት በላይ ሆኗታል፡፡
በዘመቻው 42,000 ያህል ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፡፡
ብዙዎቹም ህፃናትን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው ይባላል፡፡
እስራኤል ከአሜሪካ ወታደራዊ እርዳታ ተቀባዮች ዋነኛዋ እንደሆነች ይነገራል፡፡
ከዚያ በተጨማሪ እስራኤል በቅርቡ በሊባኖስም ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ነው፡፡
በቱኒዚያ በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ በሀላፊነት ላይ የሚገኙ ካይስ ሳኢድ ማሸነፋቸውን የምርጫው ቀዳሚ ውጤት አሳየ፡፡
እንደ ቅድሚያ ውጤቱ ካይስ ሳይድ ከተሰጠው ድምፅ ከ89 በመቶ በላይ የሚሆነው አግኝተዋል፡፡
ምርጫው የተካሄደው ከሳኢድ ካኢስ ጋር ከተፎካከሩት መካከል አንደኛው በታሰሩበት አጋጣሚ እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡
ሌላኛው እጩ ራሳቸው የፕሬዘዳንት ካይስ ሳኢድ ደጋፊ መሆናቸው ይነገራል፡፡
በቱኒዚያ ምርጫው የተካሄደው ፖለቲካዊ ውጥረት በነገሰበት ድባብ ነው፡፡
ከፖለቲካዊ ውጥረት በተጨማሪ በሀገሪቱ ምጣኔ ሐብታዊ ፈተናው እየከበደ መምጣቱ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
የእስራኤል ጦር የሄዝቦላህ ዋና ፅህፈት ቤት የጥበቃ አዛዥ የነበረውን ሱሐይል ሁሴን ሁሴይኒን ገደልኩ አለ፡፡
ሁሴይኒ የተገደለው እስራኤል ትናንት በቤይሩት በፈፀመችው ድብደባ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡
ግለሰቡ ከኢራን የጦር መሳሪያዎችን እየረከበሀ ለሔዝቦላህ የተለያዩ ክፍሎች የማከፋፈል ተልዕኮ ነበረው ተብሏል፡፡
ሔዝቦላህ ሁሴይኒ በእስራኤል ጥቃት ተገድሏል ስለመባሉ ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ አልሰጠም፡፡
እስራኤል የሊባኖስ ከባድ ድብደባዋን ከጀመረች ወዲህ የቡድኑን መሪ ሐሰን ናስላህን መግደሏ ይታወቃል፡፡
በርካታ የሄዝቦላህ ስመ ጥር የጦር መሪዎችን ግድያለሁ ማለቷን መረጃው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
Comments