መስከረም 28፣2017 - ብዙ ታካሚዎችም ህመሙን የሚያውቁት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ እንደሆነ ሀኪሞች ሲናገሩ ሰምተናል
- sheger1021fm
- Oct 8, 2024
- 1 min read
በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ካሉ አካባቢዎች የጡት ካንሰር ታመው ለህክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከሚሄዱት ውስጥ ከ 70 በመቶ በላዩ ህመማቸው 3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ነው ተባለ፡፡
4ኛ ደረጃ የካንሰር ህመም የመዳን እድሉ ከ20 እስከ 25 በመቶ ነው፡፡
ብዙ ታካሚዎችም ህመሙን የሚያውቁት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ እንደሆነ ሀኪሞች ሲናገሩ ሰምተናል፡፡
#የጡት_ካንሰር የመጀመሪያ ደረጃ ላይ እያለ ቢታወቅ ግን የመዳን እድሉ እስከ 95 በመቶ ነው ያሉት የካንሰር ህክምና እስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር የምስራች መንግስቱ ናቸው፡፡
የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች 33 በመቶ የሚሆነውን ይሸፍናል ብለዋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ሴቶችን ለበሽታ እና ለሞት ከሚዳርገው ግንባር ቀደም መንስኤዎች አንዱ ነው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ #ወጣት_ሴቶችን ጨምሮ የጡት ካንሰር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ መሆኑን ዶክተር የምስራች አስረድተዋል፡፡
የጡት ካንሰር መንስኤ ምን እንደሆነ በትክክል የሚታወቅ ባይሆንም የቤተሰብ ታሪክ፣ የሆርሞን ቴራፒ፣ ለጨረር መጋለጥ እና ሌሎች በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
ተያያዥ ዘገባን ያድምጡ… https://tinyurl.com/3v3zfjjf
Comments