መስከረም 28፣2017 - ቤንዚን በሊትር 8 ብር ከ54 ሳንቲም ጭማሪ አሳየ
- sheger1021fm
- Oct 9, 2024
- 1 min read
ቤንዚን በሊትር 8 ብር ከ54 ሳንቲም ጭማሪ አሳየ፡፡
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
በተደረገው መሻሻያ መሰረትም ቤንዚን በሊትር 8 ብር ከ54 ጭማሪ አሳይቷል፡፡
82.60 የነበረው ቤንዚን 91.14 ብር ሆኗል፡፡
ነጭ ናፍጣ 83. ብር ከ74 ሳንቲም የነበረው 6.54 ጨመሮ 90.28 ሆኗል፡፡
ኪሮሲን 83 ብር 74 የነበረው 6 ብር 54 ጨምሮ 90 ብር ከ 28 ሆኗል፡፡
ቀላል ጥቁር ናፍጣ 65.48 የነበረው 34.72 ጨምሮ 100.2 ብር ሆኗል፡፡
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 6 ብር ከ93 ሳንቲም ጨምሮ 77. 76 ሆኗል፡፡
ጭማሪው ከዛሬ 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡



Comments