top of page

መስከረም 28፣2017 - ባሳለፍነው ዓመት ሐምሌ እና ነሐሴ ወር በቴሌ ብር ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር መሰብሰቡን የገቢዎች ሚ/ር ተናገረ

ባሳለፍነው ዓመት ሐምሌ እና ነሐሴ ወር በቴሌ ብር ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


በዚህም ከ6,000 በላይ አዳዲስ ግብር ከፋዮች በቴሌ ብር እንዲከፍሉ ተደርጓል ያሉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አካሉ ጴጥሮስ ከነዚህም ግብር ከፋዮች ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ መግኘት ተችሏል ብለዋል፡፡


በተጨማም በባንክ፣ በቴሌ ብር እና በሌላ ሌላውም 25,000 በላይ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን አሳውቀዋል የተባለ ሲሆን 19,000 ገደማው ደግሞ የክፍያ ሥርዓት ፈፅመዋል ብለዋል፡፡


በዚህም በ2016 ዓ.ም ሐምሌ እና ነሐሴ ወር ብቻ ከ 237 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ተሰብስቧል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡


የገቢዎች ሚኒስቴር ግብር ከፋዮቹን ወደ ዲጂታል በማምጣት የአከፋፈል ሥርዓቱን ከወረቀት ንክኪ ውጭ ለማድረግ እየሰራ ነው የተባለ ሲሆን በዲጅታል ግብር እየከፈሉ ያሉ ደንበኞቼ ከ51,000 በላይ ደርሰዋል ብሏል፡፡


ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሁለት ወራት ከወንኩት ባለው ስራ የእቅዱን 77 በመቶ እንዳሳካም ተናግሯል፡፡


በተያዘው በጀት ዓመትም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግብር ከፋዮቹን ከወረቀት ንክኪ ውጭ በሆነ እና ማንኛውንም አገልግሎት ዲጅታላይዝድ በማድረግ ደንበኞቼን የማስተናግዳቸው ይሆናል ብሏል፡፡





ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


bottom of page