በ2017 በጀት ዓመት 700,000 ሰዎች ወደ ውጪ ሀገራት ለስራ ይላካሉ ተባለ፡፡
ይህንን ያሉት በትናንትነው ዕለት የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ናቸው፡፡
በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለ4.3 ሚሊዮን ሰዎች የስራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡

ከእነዚህ መካካልም 700,000ዎቹ በውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት የሚሰማሩ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡
በዚህ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ላይም ጥራት እና ቁጥርሩ እንዲያድግ እንዲሁም በስራ ገበያ የመረጃ አስተዳደር ላይ ይሰራል ብለዋል፡፡
ለዚህም ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ፤ በተለያዩ የስራ መስኮች ሰራተኞችን ወደተለያዩ ሀገራት እየላከች መሆኑን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተደጋግሞ ሲነገር ይሰማል።
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comments