top of page

መስከረም 28፣2017 - በየጊዜው ለሚጨምረው የሸቀጦች ዋጋ መንግስት ብዙውን ጊዜ ህገ-ወጥ ደላሎችን ሲወቅስ ይሰማል

በየጊዜው ለሚጨምረው #የሸቀጦች_ዋጋ መንግስት ብዙውን ጊዜ ህገ-ወጥ ደላሎችን ሲወቅስ ይሰማል።


በቂ ምርት አለ ዋጋ እየጨመረ ህዝብ እንዲጎዳ የሚያደርገው ህገ-ወጥ ደላላ ነው ተብሎ ተደጋግሞ ተነግሯል።


ስንዴ፣ ጤፍ፣ ሩዝ ሌላውንም ጨምሮ ከኢትዮጵያ ተርፎ ለውጭ ሀገራት የሚላክ ምርት ክልሎች አመረቱ ሲባል ቢሰማም ሸማቹ ግን ምርቱን በውድ ዋጋ ይገዛል።


ወቅትን እየጠበቁ ዋጋቸው የሚንር ሸቀጦች በቂ #ምርት ሲኖር ዋጋቸው ወደ ነበረበት አለመመለሱ የሸማቹን ወገብ ካጎበጠውም ከርሟል፡፡


ምርት የለም በሚል ሰበብ አንድ ጊዜ ዋጋቸው ከጨመረ በኋላ ምርቱ እንደልብ እየቀረበ ነው ቢባልም የሸቀጦቹ ዋጋ ወደ ነበረበት አለመመለስም ልምድ ከሆነ ቆየት ብሏል፡፡

ለምሳሌም አንድ ሰሞን ምርታቸው ከገበያ ቀንሶ የነበሩት እንደ ስንዴ እና #ጤፍ ያሉ ምርቶች ዋጋቸው ከፍ ብሎ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡


አሁን ምርቱ እንደልብ መኖሩ የሚነገር ቢሆንም ዋጋቸው ግን ተሰቅሎ ቀርቷል።


ለዚህ ችግርም ዋና መንስኤ ነው የሚባለውን ህገ-ወጥ ደላላ ተቆጣጥሮ የገበያ ሰንሰለቱ እንዲረጋጋ ማድረግ ለምን አልተቻለም?


የአዲስ አበባ #ንግድ_ቢሮ ለዚህ ችግር ከደላሎቹ ባሻገር የህገ-ወጥ ነጋዴዎች መበራከትንና የንግድ ሥርዓቱ የዘመነ አለመሆንን በምክንያትነት ያነሳል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comentarios


bottom of page