በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ለሚነሱ የግል ባይዞታዎች 5 ቢሊዮን ብር ካሳ እና 100 ሄክታር ምትክ መሬት መዘጋጀቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
በዚህኛው ምዕራፍ ከሚነሱት ውስጥ 80 በመቶው የቀበሌ ቤት፣ 10 በመቶው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቶች ነዋሪዎች እና 10 በመቶው የግል ባለይዞታዎች መሆናቸውን ከንቲባዋ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
የቀበሌ እና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ 4,000 መኖሪያ ቤቶች መዘጋጀታቸውንም ሰምተናል፡፡
ለስራ እድል ፈጠራ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ አካላት በቂ የማምረቻ፣ መሸጫ እና ምርት መያዣ ሼዶች በቀበሌ እና በንግድ በቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች ተደራጅተው የንግድ ቦታ እንዲገነቡ እንዲሁም በአነስተኛ ሱቆች ሲሰሩ ለነበሩ 500 የሱቅ ኮንቴነሮች መዘጋጀታቸውንም ከንቲባዋ ተናግረዋል።
በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት በስምንት ኮሪደሮች 132 ኪሎሜትር ርዝመት እና ከ 2,817 ሄክታር ቦታ ለማልማት ተቅዷል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት ጥናት መጠናቀቁን ፣ የዲዛይን እና ህዝብን የማወያየት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ንጋቱ ሙሉ
Comments