መስከረም 27 2018 - ‘’ሰዎችን አለመስማት፣ ለሰዎች ቅን መሆን አለመቻል፣ በስራ እና በትምህርት ውጤታማ አለመሆን የመቀንጨር ችግር ካለባቸው ሰዎች ጥቂቶቹ ምልክቶች ናቸው’’ ሀብቴ ጀቤሳ(ዶ/ር)
- sheger1021fm
- Oct 7
- 1 min read
በመቀንጭር እና ተያያዝ ችግሮች ላይ ለበርካታ ዓመታት ጥናት የሰሩት እና መጽሃፍ የጻፉት ሃብቴ ጀቤሳ (ዶ/ር) ሰዎችን አለመስማት፣ ለሰዎች ቅን መሆን አለመቻል፣ በስራ እና በትምህርት ውጤታማ አለመሆን የመቀንጨር ችግር ካለባቸው ሰዎች ጥቂቶቹ ምልክቶች እንደሆኑ ያስረዳሉ፡፡
መቀንጭር በስርዓተ ምግብ አለመስተካካል ምክንያት እንደሚከሰት የሚያስረዱት ሀብቴ ጀቤሳ(ዶ/ር) ችግሩን ለመቀነስ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም በሚፈለገው ደረጃ ችግሩ አለመቀነሱን አስረድተዋል፡፡
በሀገሪቱ ቁመታቸው እና አዕምሯቸው ከእድሚያቸው እኩል የማያድጉ ወይም የመቀንጭር ችግር ያለባቸው 37 ከመቶ ህጻናት እንደሚወለዱ ባለሞያው ጥቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ የመቀንጨርን ችግር እንደ በሽታ አለመቆጠሩ ጉዳዩ ትኩረት እንዳያገኝ ማድረጉን የሚናገሩት ባለሞያው ይህም በሀገር ልማት ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ እንዳለ ነግረውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments