መስከረም 27፣2017 - ‘’ሀይልን በብቸኝነት የመጠቀም መብት የመንግስት የፀጥታ ተቋማት ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል’’ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ
- sheger1021fm
- Oct 7, 2024
- 1 min read
የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሰየሙት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ‘’በኢትዮጵያ ምድር ሀይልን በብቸኝነት የመጠቀም መብት የመንግስት እና የመንግስት የፀጥታ ተቋማት ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል’’ ሲሉ ተናገሩ፡፡
ፕሬዘዳንቱም በተያዘው በጀት ዓመት ህገ - መንግስታዊ ሥርዓቱን በመጠበቀም የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሀላፊነቶች አፈፃፀምም የሚሻሻሉበት ይሆናሉ ብለዋል በንግግራቸው፡፡
‘’መነጋገር፣ መቀራረብ፣ መግባባት እና አብሮ መቆም የመጨረሻ ግባችን ሊሆን ይገባል’’ ሲሉ ፕሬዘዳንት አፅቀስላሴ በዛሬው የሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ተናግረዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments