መስከረም 26 2018 - ''ግጭቶችን ለመፍታት መንግስት ከሀይል ይልቅ የእርቅና የሰላም አማራጭ መንገድን መከታተሉን ይቀጥላል'' ፕሬዘዳንት ታዬ አፅቀስላሴ
- sheger1021fm
- Oct 6
- 1 min read
በየአካባቢው የሚታዩ ግጭቶችን ለመፍታት መንግስት ከሀይል ይልቅ የእርቅና የሰላም አማራጭ መንገድን መከታተሉን ይቀጥላል ተባለ፡፡
ፕሬዘዳንት ታዬ አፅቀስላሴ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን የመክፈቻ ንግግርን አድርገዋል፡፡
በመክፈቻ ንግግራቸው በተለያዩ ዘርፎች በየአመቱ ትኩረት የሚደረግባቸውን ጉዳዮች ዘርዝረዋል፡፡

ሰላምን በተመለከተም ሲያነሱ በየአካባቢው የሚታዩ ግጭቶችን በሀይል ማረቅና ማስተካከል ይቻላል ብለዋል፡፡
በየጊዜው የሚታዩ የሀይል እንቅስቃሴዎችን ለማስቆም የሚያስችል ሙሉ ዝግጁነት እና ዘመናዊ አቅም መንግስት አለው ብለዋል፡፡
የዛሬውን ግጭት በሀይል በማሸነፍ ለመጪው ትውልድ ቂም እና ቁርሾን ላለማስተላለፍ ሲባል ግን መንግስት አሁንም የእርቅና የሰላም አማራጭን ምርጫው ያደርጋል ብለዋል ፕሬዘዳንቱ በንግግራቸው፡፡
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments