መስከረም 25፣2017 - የኢሬቻ በዓል በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን ነገ ደግሞ በቢሾፍቱ ይከበራል
- sheger1021fm
- Oct 5, 2024
- 1 min read
የአዲስ አበባ ህንጻዎች፣ ጎዳናዎች አካፋይና መንገዶች ጥቁር፣ ቀይ እና ነጭ ቀለማት ለብሰዋል፡፡
ወደ ከተማ የሚያስገቡ መንገዶች አክባሪዎችን ተቀብለው አሁን ደግሞ እየሸኙ ነው፡፡
በዓሉ ኢሬቻ ነው፡፡
የምስጋና፣ የሰላም፣ የይቅርታ በዓል መሆኑ የሚነገርለት የኢሬቻ በዓል በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን ነገ ደግሞ በቢሾፍቱ ይከበራል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments