ስምምነት የተደረገውም በኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን እና በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ኤጀንሲ አሰሪዎች ፌዴሬሽን በኩል ነው።
ስምምነቱም ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት ለመሄድ ህገ-ወጥ የውጭ ሀገራት ጉዞን ለማስቀረትና በህጋዊ መንገድ የሚሄዱ ዜጎችን መረጃ ለማወቅ የሚያግዝ፣ መብት እና ደህንነታቸውንም የሚያስጠበቅ ነው ተብሏል።
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአሰሪዎቻቸው የሚደርስባቸው እንግልት እና እስራት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑም ተነግሯል።
የዚህም ዋነኛው ምክንያት ደግሞ ሰዎች በህገወጥ መንገድ በተሰማሩ የውጪ ሀገር ስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች አማካኝነት በህገ-ወጥ መንገድ ስለሚሄዱ ነው ተብሏል።
በዚህም በህገ-ወጥ መንገድ የወጡ ዜጎች በቂ መረጃ ስለሌለ እና አድራሻቸውም ስለማይታወቅ ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ እንቅፋት ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡
ፍቅሩ አምባቸው
Comentários