ጉባኤው ጥቅምት 1 እና 2 በሚሊንየም አዳራሽ ይካሄዳል ነው የተባለው።
የሥራ እና ክህሎት ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፉ ላይ ትልቅ አቅም አላት ብለዋል።
እንቆጷ ጉባኤ ሲካሄድ ይህ አቅም በመጠቀም በሀገሪቱ የሥራ እድል መፍጠር ያለመ ነው ብለዋል።
ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እንቆጷ በሚል ስያሜ የኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሺፕ ንቅናቄ ለማስጀመርና ሀገሪቱ በዘርፉ ያላትን አቅም ለሀገር ውስጥና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ማቀዱን አቶ ንጉሱ ተናግረዋል።
የሥራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ስራ ፈጣሪዎች በዕንቆጷ ጉባኤ ላይ ከባለሀብቶች ጋር እንዲገናኙ እና ሥራዎችን በጋራ የሚሰሩበት እድል የፈጠራል ሲሉ ሚንስትር ድኤታው ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፉ ያላትን አቅም በተመለከተ ከ2014 ጀምሮ ተደጋጋሚ ውይይቶች እየተደረገ ነበር የተባለ ሲሆን ከብሄራዊ የሥራ ጉባኤ ጋር ከ2 አመት በፊት ይህ ጉባኤ ተደርጎ ነበር ተብሏል።
በ2 ቀናት የእንቆጷ ጉባኤ ላይ የፓናል ውይይቶች ፣ ኤግዚቢሽን እና የሥራ ፈጣሪዎች እና ባለሀብቶች ትስስር እንዲያደርጉ ይደረጋል ተብሏል።
ለዲጂታል ዘርፉ ቅልጥፍና የመሰረተ ልማት ስራ ሟሟላት እና የማስተካከል ስራ የስራ እና ክህሎት ሚንስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ተነግሯል።
በጉባኤው ላይ የዘርፉ ምሁራን፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ አህጉራዊ ተቋማት እና አለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች ይሳተፋሉ ተብሏል።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments