top of page

መስከረም 23 2018 - ኢትዮጵያ መድሀኒት የምትቆጣጠርበት ስርዓቷ በአለም ጤና ድርጅት ተመዝኖ አንድ ደረጃ ማሻሻሏ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Oct 3
  • 1 min read

ኢትዮጵያ በአለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገራት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ምደባ(Classification) ማቹሪቲ ሌቭል ስሪ (ደረጃ 3) ላይ መድረሷ ተነግሯል፡፡


ይህ እውቅና የበዙ ጠቀሜታዎች ያሉት እንደሆነ፤ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን እና ጤና ሚኒስቴር በሰጡት የጋራ መግለጫ ላይ አስረድተዋል፡፡


በዓለም ጤና ድርጅት ኦዲተሮች በስምንት ተግባራት ላይ የሰነድ ግምገማ ተደረጎ ጥሩ የሚባል አፈፃጸም በማግኘታቸው ነው ይህ እውቅና የተገኘው ሲሉ የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ(ዶ/ር) በመድረኩ ተናግረዋል፡፡


ይህ ውጤትም ተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት፤ ለሕብረተሰቡ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ውጤታማ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የህክምና ምርቶችን ለማቅረብ የሚረዳው እና የሚያበረታው እንደሆነም የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ናቸው፡፡

ree

ኢትዮጵያ መድሀኒት የምትቆጣጠርበት ስርዓቷ በህዝብ አመኔታ እንዲኖረው ይህ እውቅና እንደሚረዳም በመድረኩ ተነስቷል፡፡


የዓለም ጤና ድርጅት አለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችና ደረጃዎች በመለኪያነት ተጠቅሞ ግምገማ በማድረግ የሀገራት ተቆጣጣሪ አካላትን ክአንድ እስከ አራት ባለው ደረጃ ገምግሞ ያስቀምጣል።

ከፍተኛ ደረጃ የሚባለው ደረጃ 4 ሲሆን ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያገኘቸው ደረጃ 3 መሆኑ ተነግሯል፡፡


ከአፍካ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ይህንን ማቹሪቲ ሌቭል ስሪ ላይ የደረሱ 9 ናቸው ተብሏል፡፡


የሀገር ውስጥ መድሀኒት አምራቾችን አቅማቸው እያደገ መምጣቱንም መቅደስ ዳባ(ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡


በዚህም መንግስት ከሚገዛው አጠቃላይ መድሀኒት፤ ከሀገር ውስጥ አምራቾች የሚገዛውን መድሀኒት 42 በመቶ ማድረሱንም ጠቁመዋል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page