top of page

መስከረም 23፣2017 - የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ በ’’ኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ’’ በዓል አከባበር ወቅት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ

  • sheger1021fm
  • Oct 3, 2024
  • 1 min read

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ እንደሚከበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናግሯል፡፡


በዚህም ከበዓሉ ዋዜማ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከታች የተጠቀሱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ለጊዜዉ ዝግ እንደሚሆኑ አስረድቷል፡፡


• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ፣


• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣


• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ፣


• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)፣


• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ ፣


• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣


• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ፣


• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ፣


• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣

• ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም፣


• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ፣


በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ የሸገር ከተማ አካባቢዎች በርካታ ህዝብ በዓሉን ለማክበር ከዋዜማው ጀምሮ ወደ ከተማችንበ ይገባሉ ብሏል ፖሊስ፡፡


በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ‘’ለጋራ ደህንነት ሲባል’’ ፍተሻ እንደሚደረግም ተናግሯል፡፡


ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ ስጡኝ ሲል ፖሊስ አሳስቧል፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page