top of page

መስከረም 23፣2017 - የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ ያገኘችው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር ከ540 በመቶ በላይ ጭማሪ አለው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Oct 3, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ ያገኘችው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር ከ540 በመቶ በላይ ጭማሪ አለው ተባለ፡፡


ይህን ያለው የብሄራዊ ባንክ ነው፡፡


የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ላይ ያደረግነው ለውጥ ያሰብነውን ግብ እየመታ ነው ብለዋል፡፡


ባለፈው ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከወርቅ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ 58 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር ተብሏል፡፡


ዘንድሮ በተመሳሳይ ወቅት ከወርቅ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ግን 488 ሚሊዮን ዶላር ነው ይህም ከ540 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል ሲሉ አቶ ማሞ ምህረቱ አስረድተዋል፡፡


ባለፈው ዓመት፤ ዓመቱን ሙሉ ወርቅን ለአለም ገበያ በማቅረብ የተገኘው ገቢ 255 ሚሊዮን ዶላር ነበር፤ ዝንድሮ ግን ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ወደ 5 መቶ ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ ገቢ ነው ብለዋል የብሄራዊ ባንክ ግዢው አቶ ማሞ ምህረቱ ፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page