የመስቀል በአል በሰፊው የሚከበርበት የጉራጌ ዞን በዘንድሮው በዓል ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር 790,000 ጎብኝዎችን በማስተናገድ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቻለሁ አለ፡፡
በዚህም በዘንድሮው የመስቀል በአል 119 ሚሊየን ብር ገደማ ተገኝቷል ያለው የዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ በዞኑ ከተዘጋጁ ገበያዎች በቀረቡ ምርቶች እና አገልግሎቶች የተሰበሰበ ነው ብሏል፡፡
በቀደሙት ዓመታት ተጓዦች በመንገዳቸው የሚያጋጥሟቸው ችግሮች እንደነበሩም የተነገረ ሲሆን ዘንድሮው ከቀናት በፊት በተከበረው የመስቀል በዓል ግን ወደ ዞኑ የሚመጡ ጎብኙዎች እንዳለፉት ዓመታት ችግሮች እንዳያጋጥማቸው አስቀድሞ ስራዎች ተሰርተዋል ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ
ፋሲካ ሙሉወርቅ
コメント