መንግስት በኮሪደር ልማት ለሚነሱ ሰዎች በቂ ጊዜ መስጠቱን ቢናገርም፤ አንዳአንድ ነዋሪዎች ግን ‘’በድንገት ነው ተነሱ የተባልነው’’ የሚሉ ቅሬታዎችን ያነሳሉ፡፡
‘’በቂ ጊዜ አልተሰጠንም፣ እንድንዘጋጅ አስቀድሞ አልተነገረንም፣ በድንገት ነው አካባቢው ለልማት ስለሚፈለግ ተነሱ የተባልነው’’ እና መሰል ቅሬታዎችን ሲያቀርቡ ይደመጣል፡፡
መንግስት በበኩሉ እንዲዘጋጁ በቂ ጊዜ ሰጥቻለው ስለጉዳዩም ከልማት ተነሺዎች ጋር መክሪያለው ብሏል፡፡
‘’ከአንድ አካባቢ የተነሳን ሰዎች በአንድ አካባቢ አልሰፈርንም ይህም ማህበራዊ ሕይወታችንን እንድናጣ አድርጎናል’’ ሲሉ ኗሪዎች ተናግረዋል መንግስት ግን ‘’በአንድ አካባቢ ነው ያሰፈርኳቸው’’ ማለቱ ይታወሳል፡፡
ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች ተመልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣው አዋጅ ምንድነው የሚለው?
የህዝብ እና የመንግስትስ መብት እንዲሁም ግዴታስ ምንድነው?

ያሬድ እንዳሻው
Comments