top of page

መስከረም 22፣2017 - አ.አ.ዩ የ2017 የት/ት ዘመን በቅድመ ምረቃ 5,300 ተማሪዎችን እንደሚቀበል ተናገረ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮ የ2017 የትምህርት ዘመን በቅድመ ምረቃ 5,300 ተማሪዎችን እንደሚቀበል ተናገረ፡፡


ይህን አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ዩኒቨርሲቲው #ራስ_ገዝ መሆኑን ተከትሎ በዘንድሮ ዓመት የሚቀበላቸው ተማሪዎችን መልምሎና ፈትኖ ማዘጋጀቱን የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዘዳንት ጄሉ ኡመር(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከሚቀበላቸው #ተማሪዎች መካከል 2,660ዎቹ በመንግስት ወጪያቸው የሚሸፈን ሲሆን የተቀሩት 2,640ዎቹ በግላቸው ከፍለው የሚማሩ ናቸው፡፡


ተማሪዎቹ የሚከፍሉት የገንዘብ መጠን እንደሚወስዱት ኮርስ የሚለያይ ሆኖ በኮርስ ከ600 ብር እስከ 2000 ብር የሚደርስ መሆኑንም ዶ/ር ጄሉ አስረድተዋል፡፡


በአጠቃላይ ከሚቀበላቸው ተማሪዎች 52 በመቶዎቹ ወንዶች ሲሆኑ 48 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡

Comments


bottom of page