ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በእጣ ደርሷቸው እና በጨረታ አሸንፈው ቤቶቹን ከተረከቡ በኋላ ያልገቡባቸው እስከ መጭው ጥቅምት 30 እንዲገቡባቸው አስጠንቅቋል፡፡
ያንን ካላደረጉም ውላቸውን አቋርጣለሁ ብሏል፡፡
ሰዎች ያፈሩትን ንብረት የመጠበቅና የማስጠበቅ ሀላፊነት ያለበት መንግስት ቤቶቹን ለመንጠቅ ህጋዊ መሰረት አለው ወይ? በጉዳዩ ላይ የህግ ባለሞያ አነጋግረናል፡፡

የህግ ባለሞያው ከነሷቸው ነጥቦች መካከል:-
• ንብረት የማፍራት መብት በህገ-መንግስቱ ከተጠቀሱት መሰረታዊ መብቶች መካከል ነው፣
• መንግስት ሰዎች ያፈሩትን መብት የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለበት፣
• መንግስት የሰዎችን ይዞታ ሊወስድ የሚችለው ወይም በንብረት መብታቸው ላይ ጣልቃ ሊገባ የሚችልበት ብቸኛ አጋጣሚ ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ከቦታው መነሳት ሲኖርባቸው ብቻ ነው፣
• በምንም ምክንያት የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸውን መንግስት መልሶ ለመንጠቅ የሚያስችል የህግ መሰረት የለውም፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments