top of page

መስከረም 22፣2015-የኢትዮጵያ ሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ እስከ መጪው ታህሳስ ወር ድረስ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመት ተሳትፎ....



የኢትዮጵያ ሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ እስከ መጪው ታህሳስ ወር ድረስ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመት ተሳትፎ መቀበልና የካፒታል ማሰባሰብ ሥራው እንደሚያጠናቅቅ ተናገረ፡፡


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የዳሬክተሮች ቦርድ ገበያውን ለመመስረት የሚያስፈልገውን 25 በመቶ ለመጋበዝ መተማመኛም ለመስጠት ከወር በፊት ወስኗል ተብሏል፡፡


በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መሰረት የተቀመጠውን የአምስት መስራቾች ቁጥር ለማሟላት ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር ያሉት 4 የልማት ድርጅቶች የኢትዮጵያ የሰነድ ነዋይ ገበያ አክሲዮን መስራች አባል ሆነው  ሆነው የኢትዮጵያ ሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ  ተቀላቅለዋል፡፡


ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር በጋራ በመመስረቻው ስምምነት ላይ የፈረሙት ኢትዮ ቴሌኮም ፣የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ፣የኢትዮጵያ መድህን ድርጅትና የብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅቶች ናቸው ተብሏል፡፡


ለገበያው የመጀመሪያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ተሰይሟል፡፡


አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ፣እሌኒ ገ/መድህን(Phd)፣ ቴዎድሮስ መኮንን(Phd) ፣ሂነጃት ሻሚል፣ፍቃዱ ፔጥሮስ፣ያስሚን ውሃብረቢ እና ህላዊ ታደሰ  ለቦርዱ ተመርጠዋል፡፡


የተሾሙት የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት ኩባንያው ሌሎች መስራች ባለሀብቶችን የመቀበል ካፒታል የማሰባሰብ ስራ አጠናቆ በሚያደርገው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ከሌሎች ተጨማሪ አባላት ጋር በድጋሚ በእጩነት ይቀርባሉ ተብሏል፡፡


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱራህማን ሰኢድ ማሂር ገበያው በኢኮኖሚ ውስጥ የሀገር ሰዎችን የምጣኔ ሐብት ተሳትፎ እንደሚያበረታ ተናግረዋል፡፡


ተህቦ ንጉሴ 


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page