top of page

መስከረም 21 2018 -በአማራ ክልል ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን የተሰራ ርብራብ እንጨት ተደርሞሶ የ30 ሰዎች ሕይወት አለፈ

  • Oct 1, 2025
  • 1 min read

መረጃውን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዣዥ ዋና ኢንስፔክተር አሕመድ ገበየሁ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነግረውታል፡፡


የአደጋው ምክንያት ለቤተክርስቲያኑ ሕንጻ ግንባታ በተሠራ የእንጨት መወጣጫ ርብራብ ላይ መሸከም ከሚችለው በላይ ሰዎች ለጉብኝት በመውጣታቸው ነው ብለዋል።


በአደጋው የ30 ሰዎች ሕይዎት ወዲያውኑ አልፏል ሲሉ ዋና ኢንስፔክተር አሕመድ አስረድተዋል።


ከ200 በላይ ሰዎች ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲኾን ይህም የሟቾችን ቁጥር ከፍ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል።


ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ርብራብ እንጨት ተደርሞሶ ሕይወታቸውን ባጡ ምእመናን የተሰማቸውን ጥልቅ ኃዘን ግልጸዋል፡፡


"የቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ ተጠናቆ ምርቃቱን በጉጉት እየጠብቀን ባለንበት ይህ አስከፊ ኀዘን በመከሰቱ ጥልቅ ኃዘን ተሰምቶናል" ብለዋል።


በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችን የቅዱሳን አምላክ ነፍሳቸውን በደጋጎቹ ቅዱሳን አባቶቻችን አጠገብ ያሳርፍልን ጉዳት ደርሶባቸው በጤና በሆስፒታል በሕክምና ለሚገኙ ወገኖቻችን ፈጣሪ በምሕረቱ እንዲጎበኛቸው እንጸልያለን ብለዋል።


Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም  ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ነሐሴ 7 2018 በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። የሃዲዱ ጠባቂ የፀጥታ አካላት የተዘጋውን መወጣጫ(ራምፕ) እንዲከፍቱላቸው ቢጠይቁም የተሰጣቸው ምላሽ እስከ ድብደባ የደረሰ

 
 
 
የነሐሴ 7 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ዩጋንዳ ዩጋንዳ ከአውሮፓ የሚባረሩ የ3ኛ አገር ስደተኞችን ልትቀበል ነው ተባለ፡፡ ዩጋንዳ ከአውሮፓ ተባራሪዎቹን ተቀብላ ለማስተናገድ መዘጋጀቷን ካቲሜሪኒ የተሰኘ የግሪክ ጋዜጣ መዘገቡን አናዶሉ ፅፏል፡፡ ጋዜጣው ዘገባውን ያሰራጨው ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን በዋቢነት በመጥቀስ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሐሳቡ ቀዳሚ አፍላቂዎች

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page