top of page

መስከረም 21፣2017 - የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ውጤት ለመቁጠር የህግ ክፍተቶችንና አሰራሩን እያጠባበቀ መሆኑን ተናግሯል

የኢትዮዽያን ገቢ እና ወጪ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ ጉልበት እንዲሆነው የተነጠፈው የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ውጤት ለመቁጠር የህግ ክፍተቶችንና አሰራሩን እያጠባበቀ መሆኑን ተናግሯል።


አክስዮን ማህበሩ ከህግ ማዕቀፍ ውጪ እስካሁን ለካሳ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍያለሁ ብሏል።


የቁም ከብቱን፣ ማዳበሪያውን፣ ፍራፍሬውንና ሌላውንም ጭነት ሀገር ለሀገር እያሳበረ የሚጓዘው ባቡር በልማድና አለም አቀፍ ህጉ እየጣሰበት የሚፈለገው ውጤት እንዳይመጣ ሲፈተን መቆየቱንም ሰምተናል።


በተነጠፈው የባቡር መንገድና ሀዲድ እክል እየገጠሙ ከፍተኛ የሀገሪቱን ገቢና ወጪ እቃዎች አዝለው የሚጓዙ ባቡሮች በሰው ባህሪና ሰው ሰራሽ ተፈጥሮ ምክንያት እየታገተ የሐገር ሐብት ሲባክን ቆይቷል ተብሏል።


ይህ ባህሪና ጠባይ አለምአቀፍ ህግና ደንብ የሚጥስ እንዲሁም ለባቡር አጠቃላይ ጭነት ስራና ትራንስፖርት ፈተና መሆኑን አክስዮን ማህበሩ ለሸገር 102.1 ራዲዮ ነግሯል።


የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር የሀገሪቱ ገቢና ወጪ ንግድ እንዲበረታ ከፍተኛ አደራ የተጣለበት መሆኑን በመረዳት ከህግና ህግ ነክ ጉዳዮች ጋር ያሉትን ክፍተቶች በማጠባበቅ፣ ከሚመለከታቸውም ጋር በህብረት ለመስራት ወገቡን እንደታጠቀም ሰምተናል።


ተህቦ ንጉሴ

Comentarios


bottom of page